የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት 138 ሺህ 736 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረጉን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው አስታወቁ።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው እንዳስታወቁት፣ በሩብ ዓመቱ የተመዘገበው ውጤት ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ29.4 በመቶ ዕድገት አሳይቷል። ይህም ተቋሙ የኤሌክትሪክ አገልግሎትን ለተጨማሪ ዜጎች ለማዳረስ እያደረገ ያለው ጥረት ውጤት ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል።
የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ  ከሆኑ አዳዲስ ደንበኞች መካከል 123 ሺህ 509 የሚሆኑት የቅድመ ክፍያ (Prepaid)፣ 15 ሺህ 227 ደግሞ የድህረ ክፍያ (Postpaid) ሥርዓት ተጠቃሚዎች ናቸው።
አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወነው ሥራ፣ ከዋናው የኤሌክትሪክ ግሪድ (On-grid) 21፣ ከኦፍግሪድ ውጭ (Off-grid) ደግሞ 9፣ በድምሩ 30 ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ መሆናቸውን ኢንጂነር ጌቱ ገልጸዋል። ይህ ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ15.4 በመቶ ዕድገት አሳይቷል።
ለነባር ደንበኞች አስተማማኝ የኃይል አቅርቦትን ለማረጋገጥ 630 ኪ.ሜ የዲስትሪቢዩሽን ኔትወርክ መልሶ የግንባታ እንዲሁም 275 የዲስትሪቢዩሽን ትራንስፎርመሮችን የማሻሻል ሥራ መከናወኑንም ገልጸዋል።
አዳዲስ ደንበኞችን እንዲሁም የገጠር ከተሞችና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ 1 ሺህ 730 ኪሎ ሜትር የዲስትሪቢዩሽን ኔትወርክ ማስፋፊያ እንዲሁም 1 ሺህ 329 አዳዲስ የዲስትሪቢዩሽን ትራንስፎርመሮችን ተከላ ሥራ መከናወኑን ተናግረዋል።
በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የተመዘገበው የደንበኞች ቁጥር ዕድገት፣ ተቋሙ የአሌክትሪክ ተደራሽነትን እውን ለማድረግ በያዘው ዕቅድ መሠረት የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ የጀመረውን ጥረት የሚያመለክት መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል። በቀጣይም የደንበኞችን ቁጥር በማሳደግ የዓመቱን ዕቅድ ማሳካት የተቋሙ ዋነኛ የሥራ አቅጣጫ መሆኑን አስረድተዋል።
ተቋሙ ቀልጣፋ አገልግሎት ከመስጠትና አስተማማኝ የኃይል አቅርቦትን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን፣ ብልሹ አሠራርን ለመከላከልና ተጠያቂነትን ለማስፈን እየሠራ መሆኑንም ተገልጿል። በዚህ ረገድ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት በዲጂታልና በሌሎች አማራጮች 96 ጥቆማዎችና አቤቱታዎች ቀርበዋል። ከእነዚህ ውስጥ 85ቱ ላይ የማጣራት ሥራ የተከናወነ ሲሆን 11ዱ በምርመራ ሂደት ላይ እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡
በተከናወነው ምርመራ 42 ሠራተኞች ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል። በ29 ሠራተኞች ላይም የተለያዩ አስተዳድራዊ እርምጃዎች መወሰዳቸው ተገልጿል። ከተዘረዘሩት እርምጃዎች መካከል 4 የጽሑፍ ማስጠንቀቂያዎች፣ 19 የደመወዝ ቅጣቶችና 1 የሥራ ስንብት ይገኙበታል። በተጨማሪም 5 ሠራተኞች ከተደረገው ምርመራ ነፃ መባላቸውን ሲገለጽ፣ ቀሪዎቹ ጉዳዮች በሂደት ላይ እንደሚገኙ ተመልክቷል።
በአጠቃላይ፣ ተቋሙ በሩብ ዓመቱ የተሻለ የሥራ አፈጻጸም ማስመዝገቡን ኢንጂነር ጌቱ ገልጸዋል። በዲጂታል የክፍያ ሥርዓት ወርሃዊ ሂሳባቸውን የሚከፍሉ ደንበኞች መጠን 95.3 በመቶ መድረሱን፣ እንዲሁም የተቋሙ አጠቃላይ ደንበኞች ብዛት 6.03 ሚሊዮን መድረሱን አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በዛሬው ዕለት አካሂዷል።
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት